ወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ አስመልክቶ የተደረገ የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ

የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው አማራና አፋር ክልሎች ጤና ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የመጀመሪያ ዙር የ50ሺህ ብር ገንዘብ ድጋፍ አደረገ ፡፡የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አማኑኤል ጌታቸው ገንዘቡን ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት የዜጎች ከአካባቢያቸው መፈናቀል ፤ የንብረት እና የሰው ሕይወት መጥፋት እንደደረሰ ገልጸው እንደህብረተሰብ አካል የማህበሩ አባላት ከሚያዋጡትና ከአጋር ድርጅቶች ከተሰበሰበ የማህበሩ ስራ ማስኬጃ በጀት ላይ ለመጀመሪያ ዙር 50 ሺህ ብር በቸክ ለታለመው አላማ እንዲውል አስረክበዋል ፡፡አያይዘውም አቶ አማኑኤል ማህበራቸው ህዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ከመንግስት እና ከህዝብ ጎን መሆን በሚያስፈልግበት ጊዜ ሃላፊነቱን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው ድጋፉ በቀጣይም ጊዜም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋም ለተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ላቀረብነው የድጋፍ ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፉ በአፋርና በአማራክልል የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ላለው ተግባር እንደሚውልም ገልጸዋል ፡፡