እድሜዎ ከ40-70 መካከል ነው? እንግዲያውስ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መስፈርቶችን አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን የሚያሟሉ ከሆነ የሳንባ ካንሰር ምርመራ ያስፈልጎታል!

    1. ሲጋራ ያጨሳሉ / የቀደመ የማጨስ ታሪክ አሎት? :- ቢያንስ በቀን 1 ፓኮ ሲጋራ ከ 10 ዐመታት በላይ ወይም በቀን 2 ፓኮ ሲጋራ ከ 5 ዐመታት በላይ ወይም ከ 5 ዐመታት ያጨሱ ከሆነ፤
    2. ሽሻ ያጨሳሉ / የቀደመ የማጨስ ታሪክ አሎት? :- በሳምንት አንድ ጊዜ ለ10 ዐመታት እና ከዛ በላይ ሽሻ የሚያጨስ
    3. ሲጋራ ከሚያጨሱ ስዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት እና ተጋላጭነት አለዎት? :- ሲጋራ ከሚያጨሱ ሰዎች ጋር ከ20 ዓመት በላይ የጠበቀ ቅርበት ካለ፤ ለምሳሌ የቤተሰብ አባል፣ የስራ ባልደረባ ወይም ሌላ
    4. የካንሰር በሽታ ታመው ያውቃሉ? :- ቀደም ሲል በህክምና የተረጋገጠ እና የዳነ የካንሰር በሽታ እንዳለብዎት ከታወቀ
    5. በቤተሰብዎ ውስጥ በሳንባ ካንሰር የታመመ ሰው ያውቃሉ? :- የቤተሰብ አባል (ወላጅ፣ ወንድም ፣እህት እና ልጆች) በሳንባ ካንሰር ታመው የሚያውቁ ከሆነ
    6. ከዚህ በፊት የቲቢ/የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ተገኝቶብዎት ያውቃል? :- የቲቢ/የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ከታከሙ ሶስት ዓመትና ከዛ በላይ ከሆነ
    7. የኤችአይቪ ቫይረስ ምርመራ አድርገው ያውቃሉ? :- ኤችአይቪ ቫይረስ በደም ውስጥ ከተገኘና ለ10 ዐመታት እና ከዛ በላይ የፀረ-ኤችአይቪ መድሃኒት ከወሰዱ
    8. ሥር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት በሽታ (COPD) ታክመው ያውቃሉ? :- በጤና ተቋም ከተረጋገጠ ወይም የ “COPD” ዋና ዋና ምልክቶች (የትንፋሽ ማጠር የማያቋርጥ ሳል ከ አክታ/ያለ-አክታ፣ ሲር ሲር የሚል ድምጽ እና ለመተንፈስ መቸገር) ቢያንስ ለ 2 ዓመታት ከታዩ
    9. ለማብሰል የእንስሳት/የእፅዋት የምግብ ማብሰያ ግብአቶችን እንደ እንጨት፣ ኩበት፣ ከሰል የመሳሰሉትን ይጠቀማሉ? :- በተጠቀሱት መንገዶች ምግብ ለማብሰል በቀን ለ2 ሰዓታት እና ከዚያ በላይ ለ10 ዐመት እና ከዚያ በላይ ከተጠቀመ
    10. አሁን በሚሰሩት ወይም ከዚህ ቀደም በተሰማሩበት ስራ ለጭስ ወይም ጥቀርሻ ተጋላጭነት አለዎት? :- ከ10 ዓመታት እና ከዛ በላይ የቆየ የአርሰኒክ፣ የቤሪልየም፣ ሲሊካ፣ አስቤስቶስ ወይም የብረት ማቃጠል/ማቅለጥ ሂደት የሚኖር ጭስ/ጥቀርሻ ተጋላጭነት ካለ

ለበለጠ መረጃ ወደ [email protected] ውጤትዎን በመግለፅ ነፃ የሳንባ ካንሰር ምርመራ እንዲያገኙ ማድረግ ይቻላል!

የሳንባ ካንሰር ተጋላጭነት ቅድመ ምርመራ

እድሜዎ ከ40-70 መካከል ነው? እንግዲያውስ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መስፈርቶችን አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን የሚያሟሉ ከሆነ የሳንባ ካንሰር ምርመራ ያስፈልጎታል! ሲጋራ ያጨሳሉ / የቀደመ የማጨስ ታሪክ

Read More »